7 አንተ ስለምትመልስልኝ፣በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።
8 ጌታ ሆይ፤ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤ከአንተም ሥራ ጋር የሚወዳደር ሥራ የለም።
9 ጌታ ሆይ፤ አንተ የሠራሃቸው ሕዝቦች ሁሉ፣መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ፤ለስምህም ክብር ይሰጣሉ፤
10 አንተ ታላቅ ነህና፤ ታምራትም ትሠራለህ፤አንተ ብቻህን አምላክ ነህ።
11 እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤በእውነትህም እሄዳለሁ፤ስምህን እፈራ ዘንድ፣ያልተከፋፈለ ልብ ስጠኝ።
12 ጌታ አምላኬ ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ፤
13 ለእኔ ያሳየሃት ምሕረት ታላቅ ናትና፤ነፍሴንም ከሲኦል ጥልቀት አውጥተሃል።