1 አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በቀንና በሌሊት በፊትህ አጮኻለሁ።
2 ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፤
3 ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤ሕይወቴም ወደ ሲኦል ተቃርባለች።
4 ወደ ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር ተቈጠርሁ፤ዐቅምም አጣሁ።