21 እጄ ይደግፈዋል፤ክንዴም ያበረታዋል።
22 በጠላት አይበለጥም፤ክፉ ሰውም አይበግረውም።
23 ባላንጣዎቹን በፊቱ አደቅቃቸዋለሁ፤ጠላቶቹንም እቀጠቅጣለሁ።
24 ታማኝነቴና ምሕረቴ ከእርሱጋር ይሆናል፤በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።
25 እጁን በባሕር ላይ፣ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።
26 እርሱም፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤አምላኬና መዳኛ ዐለቴም ነህ’ ብሎ ይጠራኛል።
27 እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፤ከምድር ነገሥታትም በላይ ከፍ ይላል።