30 “ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ደንቤን ባይጠብቁ፣
31 ሥርዐቴን ቢጥሱ፣ትእዛዜንም ባያከብሩ፣
32 ኀጢአታቸውን በበትር፣በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።
33 ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፤ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።
34 ኪዳኔን አላፈርስም፤ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።
35 አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣ዳዊትን አልዋሸውም።
36 የዘር ሐረጉ ለዘላለም፣ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሓይ ጸንቶ ይኖራል፤