33 ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፤ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።
34 ኪዳኔን አላፈርስም፤ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።
35 አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣ዳዊትን አልዋሸውም።
36 የዘር ሐረጉ ለዘላለም፣ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሓይ ጸንቶ ይኖራል፤
37 በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው፣እንደ ጨረቃ እርሱ ለዘላለም ይመሠረታል።” ሴላ
38 አሁን ግን ናቅኸው፤ ጣልኸውም፤የቀባኸውንም እጅግ ተቈጣኸው።
39 ከባሪያህ ጋር የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ፤የክብር ዘውዱን ትቢያ ላይ ጥለህ አቃለልኸው።