40 ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፤ምሽጉንም ደመሰስህ።
41 ዐላፊ አግዳሚው ሁሉ ዘረፈው፤ለጎረቤቶቹ መዘባበቻ ሆነ።
42 የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረግህ፤ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው።
43 የሰይፉን ስለት አጠፍህ፤በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም።
44 ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው።
45 የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው፤ዕፍረትንም አከናነብኸው። ሴላ
46 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን?ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?