5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤
6 በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋር ማን ሊስተካከል ይችላል?ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?
7 እግዚአብሔር በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በጣም የሚፈራ፣በዙሪያውም ካሉት ሁሉ በላይ እጅግ የሚከበር ነው።
8 የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ታማኝነትህም ከብቦሃል።
9 የባሕርን ቍጣ ትቈጣጠራለህ፤ሞገዱም ሲነሣ ጸጥ ታደርገዋለህ።
10 አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።
11 ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤ዓለምንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አንተ መሠረትህ።