1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል።
2 እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።
3 እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።
4 በላባዎቹ ይጋርድሃል፤በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።
5 የሌሊትን አስደንጋጭነት፣በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤
6 በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም።
7 በአጠገብህ ሺህ፣ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃል፤ወደ አንተ ግን አይቀርብም።