13 በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
14 “ወዶኛልና እታደገዋለሁ፤ስሜን አውቆአልና እከልለዋለሁ።
15 ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።
16 ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”