5 የሌሊትን አስደንጋጭነት፣በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤
6 በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም።
7 በአጠገብህ ሺህ፣ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃል፤ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
8 በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ።
9 እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።
10 ክፉ ነገር አያገኝህም፤መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤
11 በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋልና።