12 ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ።
13 በእግዚአብሔር ቤት ተተክለዋል፤በአምላካችንም አደባባይ ይንሰራፋሉ።
14 ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ፤እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ።
15 “እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤እርሱ ዐለቴ ነው፤ በእርሱ ዘንድ እንከን የለም” ይላሉ።