3 ዐሥር አውታር ባለው በገና፣በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው!ሐሳብህስ ምን ያህል ጥልቅ ነው!
6 ደነዝ ሰው ይህን አያውቅም፤ነኁላላም አያስተውለውም።
7 ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣ለዘላለሙ ይጠፋሉ፤
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም ልዑል ነህ።
9 ጠላቶችህ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፤ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ።