2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ።
4 ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ፣ከባሕርም ሞገድ ይልቅ፣ከፍ ብሎ ያለው እግዚአብሔር ኀያል ነው።
5 ሥርዐትህ የጸና ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣ቤትህ በቅድስና ይዋባል።