1 በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ”ለምን ትሏታላችሁ?
2 ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ?“ክፉዎች፣ እነሆ፣ ቀስታቸውን ገትረዋል፤የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።
3 መሠረቱ ከተናደ፣ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል?”
4 እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው።ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
5 እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጥኡን ይመረምራል፤ዐመፃን የሚወዱትን ግን፣ነፍሱ ትጠላቸዋለች።
6 እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።