1 ጒልበቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ እወድሃለሁ።
2 እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው።
3 ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ከጠላቶቼም እድናለሁ።
4 የሞት ገመድ አነቀኝ፤የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ።
5 የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።