1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህአትገሥጸኝ፤በመዓትህም አትቅጣኝ።
2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ።
3 ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤እስከ መቼ፤ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል?
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤
5 በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል?