1 አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
2 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ፣ይፈሩ፤ ሁከትም ይምጣባቸው፤ የእኔን መጐዳት የሚመኙ፣በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
3 በእኔ ላይ፣ “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ፣ተሸማቀው ወደ ኋላ ይመለሱ።
4 ነገር ግን የሚሹህ ሁሉ፣በአንተ ሐሤት ያድርጉ፤ ደስም ይበላቸው፤“ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ሁል ጊዜ፣እግዚአብሔር ከፍ ይበል!” ይበሉ።
5 እኔ ግን ምስኪንና ችግረኛ ነኝ፤አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ረዳቴም፣ ታዳጊዬም አንተ ነህና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አትዘግይ።