1 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ይሰማኝም ዘንድ ወደ አምላክ ጮኽሁ።
2 በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ነፍሴም አልጽናና አለች።
3 አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች። ሴላ
4 ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ።