2 በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ደምቀህ ታይ።ኀይልህን አንቀሳቅስ፤መጥተህም አድነን።
3 አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።
4 የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በሕዝብህ ጸሎት ላይ ቍጣህ የሚነደው፣እስከ መቼ ድረስ ነው?
5 የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።
6 ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን።
7 የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።
8 ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ፤አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት።