10 አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።
11 ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤ዓለምንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አንተ መሠረትህ።
12 ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርህ አንተ ነህ፤ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ሐሤት ያደርጋሉ።
13 አንተ ክንደ ብርቱ ነህ፤እጅህ ኀያል ናት፤ ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለች ናት።
14 ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤ምሕረትና ታማኝነት በፊትህ ይሄዳሉ።
15 እግዚአብሔር ሆይ፤ እልልታን የሚያውቅ፣በፊትህም ብርሃን የሚሄድ ሕዝብ ምስጉን ነው።
16 ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል፤በጽድቅህም ሐሤት ያደርጋሉ፤