2 ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁና።
3 አንተም እንዲህ ብለሃል፤ “ከመረጥሁት ጋር ኪዳን ገብቻለሁ፤ለባሪያዬ ለዳዊት ምያለሁ፤
4 ‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤
6 በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋር ማን ሊስተካከል ይችላል?ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?
7 እግዚአብሔር በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በጣም የሚፈራ፣በዙሪያውም ካሉት ሁሉ በላይ እጅግ የሚከበር ነው።
8 የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ታማኝነትህም ከብቦሃል።