1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ፣ሰው ብፁዕ ነው።
2 ነገር ግን ደስ የሚሰኘው በእግዚአብሔር ሕግ ነው፤ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል።
3 እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
4 ክፉዎች ግን እንዲህ አይደሉም፤ነገር ግን ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው፣ገለባ ናቸው።