15 የክፉውንና የበደለኛውን ክንድ ስበር፤የእጁንም ስጠው፤ምንም እስከማይገኝ ድረስ።
16 እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው፤ሕዝቦችም ከምድሩ ይጠፋሉ።
17 እግዚአብሔር ሆይ፤ የተገፉትን ምኞት ትሰማለህ፤ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጆሮህንም ወደ እነርሱ ጣል ታደርጋለህ፤
18 ከዐፈር የተፈጠረ ሰው ከእንግዲህእንዳያስጨንቃቸው፣አንተ ለድኻ ዐደጉና ለተገፋው ትሟገታለህ።