21 የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ።
22 ፀሓይ በወጣች ጊዜም ይመለሳሉ፤በየጐሬአቸውም ገብተው ይተኛሉ።
23 ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል።
24 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው!ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች።
25 ይህች ባሕር ሰፊና የተንጣለለች ናት፤ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ስፍር ቍጥር የሌላቸውም ነፍሳት በውስጧ አሉ።
26 መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል።
27 ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸው ዘንድ፣እነዚህ ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።