1 አምላክ ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤እዘምራለሁ፤ በፍጹም ነፍሴም እዘምራለሁ።
2 በገናም መሰንቆም ተነሡ፤እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤በሕዝቦችም መካከል እዘምርልሃለሁ።
4 ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ትደርሳለች።
5 አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።
6 ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣በቀኝ እጅህ ታደግ፤ መልስልኝም።