4 እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው።ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
5 እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጥኡን ይመረምራል፤ዐመፃን የሚወዱትን ግን፣ነፍሱ ትጠላቸዋለች።
6 እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።
7 እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤የጽድቅ ሥራም ይወዳል፤ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።