1 ሃሌ ሉያ።በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።
2 የእግዚአሔር ሥራ ታላቅ ናት፤ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።
3 ሥራው ባለ ክብርና ባለ ግርማ ነው፤ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
4 ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤ እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው።
5 ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።
6 ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣የአሠራሩን ብርታት አሳይቶአል።