11 እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤“ከገዛ ራስህ ፍሬ፣በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።
12 ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣ለዘላለም ይቀመጣሉ።
13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፣ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወዶአልና እንዲህ አለ፤
14 “ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ።
15 እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ፤ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ።
16 ለካህናቷ ድነትን አለብሳለሁ፤ቅዱሳኗም በደስታ ይዘምራሉ።
17 “በዚህም ለዳዊት ቀንድ አበቅላለሁ፤ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ።