3 የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።
4 የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!
5 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ።
6 ሳላስታውስሽ ብቀር፣ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣ምላሴ ከትናጋዬ ጋር ትጣበቅ።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤ደግሞም፣ “አፍርሷት፤ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።
8 አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሺው ድርጊት፣የእጅሽን የሚሰጥሽ የተመሰገነ ነው፤
9 ሕፃናትሽንም ይዞ፣በዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ የተመሰገነ ነው።