3 ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤በአንድ ላይም ብልሹ ሆነዋል፤አንድ እንኳ፣መልካም የሚያደርግ የለም።
4 የእግዚአብሔርን ስም የማይጠሩት፣ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ዕውቀት የላቸውምን?
5 ባሉበት ድንጋጤ ውጦአቸዋል፤እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና።
6 እናንተ የድኾችን ዕቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን መጠጊያቸው ነው።
7 ምነው እስራኤልን የሚያድን ከጽዮን በወጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።