1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ልመናዬን አድምጥ፤በታማኝነትህና በጽድቅህም፣ሰምተህ መልስልኝ።
2 ሰው ሆኖ በፊትህ ጻድቅ የለምና፣ባሪያህን ወደ ፍርድ አታቅርበው።
3 ጠላት እስከ ሞት አሳዶኛል፤ሕይወቴንም አድቅቆ ከዐፈር ቀላቅሎአል፤ቀደም ብለው እንደ ሞቱትም፣በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል።
4 ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ዝላለች፤ልቤም በውስጤ ደንግጦአል።
5 የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ፤ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤የእጅህንም ሥራ አውጠነጠንሁ።
6 እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች። ሴላ
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጥነህ መልስልኝ፤መንፈሴ ደከመች፤ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፣ፊትህን ከእኔ አትሰውር።