1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?በተቀደሰው ኰረብታህስ ማን መኖር ይችላል?
2 አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ጽድቅን የሚያደርግ፤ከልቡ እውነትን የሚናገር፤
3 በምላሱ የማይሸነግል፤በባልንጀራው ላይ ክፉ የማይሠራ፤ወዳጁን የማያማ፤
4 ነውረኛ በፊቱ የተናቀ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፤ዋጋ የሚያስከፍለውም ቢሆን፣ቃለ መሐላውን የሚጠብቅ፤
5 ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር፣በንጹሓን ላይ ጒቦ የማይቀበል፤እነዚህን የሚያደርግ፣ከቶ አይናወጥም።