6 በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ጩኸቴም ከፊቱ ደረሰ፤ ወደ ጆሮውም ገባ።
7 ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤የተራሮችም መሠረት ተናጋ፤ጌታ ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።
8 ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤የሚባላ እሳት ከአፉ፤የፍም ነበልባል ከእርሱ ፈለቀ።
9 ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ከእግሩም በታች ጥቍር ደመና ነበረ።
10 በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤በነፋስም ክንፍ መጠቀ።
11 ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤በዝናብ አዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ።
12 በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣ደመናት፣ የበረዶ ድንጋይና መብረቅ ወጡ።