6 መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤ዑደቱም እስከ ሌላኛው ዳርቻ ነው፤ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።
7 የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤ የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል።
8 የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ዐይንን ያበራል።
9 እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው፤ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍርድ የታመነ፣ሁለንተናውም ጻድቅ ነው፤
10 ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል።
11 ደግሞም አገልጋይህ በእርሱ ጥንቃቄ ያደርጋል፤እርሱንም መጠበቅ ወሮታ አለው።
12 ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል?ከተሰወረ በደል አንጻኝ።