3 ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣ልቤ አይፈራም፤ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ልበ ሙሉ ነኝ።
4 እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤እርሷንም እሻለሁ፤ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።
5 በመከራ ቀን፣በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤
6 በዚህ ጊዜ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ፣ራሴ ከፍ ከፍ ይላል፤በድንኳኑም ውስጥ የእልልታ መሥዋዕት እሠዋለሁ፤ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤እዘምርለታለሁም።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤ራራልኝ፤ ስማኝም።
8 “ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤ልቤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።
9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤መቼም ረዳቴ ነህና።አዳኝ አምላኬ ሆይ፤አትጣለኝ፤ አትተወኝም።