5 በመከራ ቀን፣በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤
6 በዚህ ጊዜ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ፣ራሴ ከፍ ከፍ ይላል፤በድንኳኑም ውስጥ የእልልታ መሥዋዕት እሠዋለሁ፤ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤እዘምርለታለሁም።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤ራራልኝ፤ ስማኝም።
8 “ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤ልቤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።
9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤መቼም ረዳቴ ነህና።አዳኝ አምላኬ ሆይ፤አትጣለኝ፤ አትተወኝም።
10 አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር ይቀበለኛል።
11 እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤ስለ ጠላቶቼም፣በቀና መንገድ ምራኝ።