2 ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
3 የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤ እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።
4 የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው።
5 የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል።
6 ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣ስርዮንንም እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።
7 የእግዚአብሔር ድምፅየእሳት ነበልባል ይረጫል።
8 የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤ የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።