1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ!
2 ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔርአይታደግሽም” አሏት። ሴላ
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬንየምትከልል ጋሻ ነህ፤ክብሬና፣ ራሴንም ቀና ቀናየምታደርግ አንተ ነህ።
4 ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ፤እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ
5 እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ።