1 እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ።
2 ከሚውጥ ጒድጓድ፣ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤አካሄዴንም አጸና።
3 ለአምላካችን የሚሆን ውዳሴ፣አዲስ ዝማሬን በአፌ ላይ አኖረ፤ብዙዎች ያያሉ፤ ይፈራሉም፤ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
4 እግዚአብሔርን መታመኛው ያደረገ፣ወደ ትዕቢተኞች የማይመለከት፣የሐሰት አማልክትን ወደሚከተሉት የማያይ፣ሰው ብፁዕ ነው።
5 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤ለእኛ ያቀድኸውን፣ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ላውራው ልናገረው ብል፣ስፍር ቍጥር አይኖረውም።