4 እግዚአብሔርን መታመኛው ያደረገ፣ወደ ትዕቢተኞች የማይመለከት፣የሐሰት አማልክትን ወደሚከተሉት የማያይ፣ሰው ብፁዕ ነው።
5 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤ለእኛ ያቀድኸውን፣ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ላውራው ልናገረው ብል፣ስፍር ቍጥር አይኖረውም።
6 መሥዋዕትንና ቊርባንን አልፈለግህም፤ጆሮቼን ግን ከፈትህ፤የሚቃጠል መሥዋዕትን፣የኀጢአትንም መሥዋዕት አልሻህም።
7 እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ መጥቻለሁ፤ስለ እኔ በመጽሐፍ ተጽፎአል፤
8 አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።”
9 በታላቅ ጉባኤ ውስጥ ጽድቅን አበሠርሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እንደምታውቀው፣ከንፈሮቼን አልገጠምሁም።
10 ጽድቅህን በልቤ አልሸሸግሁም፤ታማኝነትህንና ማዳንህን እናገራለሁ፤ምሕረትህንና እውነትህን፣ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።