1 አምላክ ሆይ፤ በጆሮአችን ሰምተናል፤አባቶቻችን በቀድሞ ዘመን፣እነርሱ በነበሩበት ዘመን፣ያደረግኸውን ነግረውናል።
2 ሕዝቦችን በእጅህ አሳደህ አወጣሃቸው፤አባቶቻችንን ግን ተከልሃቸው፤ሕዝቦችን አደቀቅህ፤አባቶቻችንን ግን ነጻ አወጣሃቸው።
3 ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤አንተ ወደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ንጉሤ ነህ፤ያዕቆብም ድል እንዲያደርግ የወሰንህ አንተ ነህ።
5 በአንተ ጠላቶቻችን በመጡበት እንዲመለሱ እናደርጋለን፤በስምህም ባላጋራዎቻችንን ከእግራችን በታች እንረግጣለን።
6 በቀስቴ አልተማመንም፤ሰይፌም አያስጥለኝም።