3 ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤አንተ ወደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ንጉሤ ነህ፤ያዕቆብም ድል እንዲያደርግ የወሰንህ አንተ ነህ።
5 በአንተ ጠላቶቻችን በመጡበት እንዲመለሱ እናደርጋለን፤በስምህም ባላጋራዎቻችንን ከእግራችን በታች እንረግጣለን።
6 በቀስቴ አልተማመንም፤ሰይፌም አያስጥለኝም።
7 አንተ ግን በጠላቶቻችን ላይ ድልን ትሰጠናለህ፤ባላንጣዎቻችንንም ታሳፍራለህ።
8 ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን። ሴላ
9 አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም።