6 አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይኖራል፤የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ናት።
7 ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።
8 ልብስህ ሁሉ በከርቤ፣ በአደስና በጥንጁት መዐዛ ያውዳል፤በዝኆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶችም፣የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኙሃል።
9 ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።
10 ልጄ ሆይ፤ አድምጪ፤ አስተዉይ፤ ጆሮሽንም አዘንብይ፤ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።
11 ንጉሥ በውበትሽ ተማርኮአል፤ጌታሽ ነውና አክብሪው።
12 የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።