1 ቂል በልቡ፣“እግዚአብሔር የለም” ይላል።ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤በጎ ነገርን የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም።
2 በማስተዋል የሚመላለስ፣እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣እግዚአብሔር ከሰማይ፣ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3 ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤በአንድነትም ተበላሹ፤አንድ እንኳ፣በጎ የሚያደርግ የለም።
4 ሰው እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉት፣እግዚአብሔርንም ጠርተው የማያውቁት፣እነዚያ ክፉ አድራጊዎች ከቶ አይማሩምን?