1 እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል።
2 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤በትዕቢት የሚዋጉኝ ብዙዎች ናቸውና።
3 ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።
4 ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
5 ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ።