3 ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤እስከ መቼ፤ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል?
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤
5 በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል?
6 ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ፤ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።
7 ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኖአቸዋል።
8 እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቶአልና።
9 እግዚአብሔር ልመናዬን አድምጦአል፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል።