4 በድንኳንህ ለዘላለም ልኑር፤በክንፎችህም ጥላ ልከለል። ሴላ
5 አምላክ ሆይ፤ ስእለቴን ሰምተሃልና፤ስምህን የሚፈሩትንም ሰዎች ርስት ለእኔ ሰጠህ።
6 የንጉሡን ዕድሜ አርዝምለት፤ዘመኑንም እስከ ብዙ ትውልድ ጨምርለት፤
7 በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ይንገሥ፤ይጠብቁት ዘንድ ምሕረትህንና ታማኝነትህን አዘጋጅለት።
8 ስለዚህ ለስምህ ዘወትር ውዳሴ አቀርባለሁ፤ስእለቴንም በየጊዜው እፈጽማለሁ።