1 ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ድነቴም የሚመጣልኝ ከእርሱ ዘንድ ነው።
2 ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።
3 ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው?ይህን የዘመመ ግድግዳ፣ የተንጋደደ ዐጥር፣ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትሻላችሁ?
4 ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤በአፋቸው ይመርቃሉ፤በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ
5 ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ነውና።
6 ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።