4 ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤በአፋቸው ይመርቃሉ፤በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ
5 ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ነውና።
6 ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።
7 መዳኔና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ብርቱ ዐለቴና መሸሸጊያዬ በእግዚአብሔር ነው።
8 ሰዎች ሆይ፤ ሁል ጊዜ በእርሱ ታመኑ፤ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ
9 ከተናቀ ወገን መወለድ ከንቱ፣ከከበረውም መወለዱ ሐሰት ነው።በሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም፣ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው።
10 በዝርፊያ አትታመኑ፤በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤በዚህ ብትበለጽጉም፣ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።