1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤ለአንተ የተሳልነውን እንፈጽማለን።
2 ጸሎትን የምትሰማ ሆይ፤የሰው ልጆች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ።
3 ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ።
4 አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣በአደባባይህም ያኖርኸው ምስጉን ነው!ከተቀደሰው መቅደስህ፣ከቤትህም በረከት እንረካለን።
5 እግዚአብሔር አዳኛችን ሆይ፤በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣በርቀት ላለውም ባሕር ተስፋ ነህ።
6 ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ኀይልንም ታጥቀሃል።